Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ 6 ነጥብ 6 ሚሊየን የእጅ ጓንቶችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ 6 ነጥብ 6 ሚሊየን የእጅ ጓንቶች ድጋፍ ማድረጉን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ አስታወቁ።
ከኮሮና ቫይረስ መከሰት በኋላ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ድጋፍ ያደረገው።
የተደረገው የእጅ ጓንት ድጋፍ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ላይ ግንባር ቀደም ሚና እየተወጡ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በጤና ሚኒስቴር በኩል ይሰራጫል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ከዚህ ቀደም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በ40 ሚሊየን ብር የገዛቸውን የመጀመሪያ ዙር የህክምና መርጃ ቁሳቁሶችን ለጤና ሚኒስቴር ማስረከቡ የሚታወስ ነው።
Exit mobile version