አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የደመራና የመስቀል አከባበር ሥነ-ሥርዓት በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ ላደረጉ ተቋማት እና ግለሰቦች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጸጥታው ዘርፍ ላደረገው ጥረት፣ እንዲሁም ዜጎች በሰላማዊ መንገድ በዓሉ እንዲከበር ላሳዩት ሥነ-ምግባር እና ቆራጥነት በአርዓያነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል።
ወጣቶች ለበዓሉ ድምቀትና ሰላም ያሳዩት ትጋት በሌላም ነገር እንደሚደግሙት አምናለሁ ሲሉ ነው የገለጹት፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጨረሻም ሰላም ለመጠበቅ እና ለማስጠበቅ በመተባበርና በመቀናጀት ከመስራት የተሻለ ውጤታማ መንገድ የለም ሲሉ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡