Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 90ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።
በዚህም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ በ1954ቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።
በተመሳሳይ የግልግል ዳኝነትን እና የዕርቅ አሠራር ሥነ ሥርዓት ረቂቅ አዋጅ እንዲሁም የአክሬዲቴሽን አገልግሎት ክፍያ ረቂቅ ደንብን ጨምሮ በልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በተለይም የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጁ መሻሻሉ በፌደራል ሥርዓት ውስጥ የሚና እና የኃላፊነት ክፍፍል በአግባቡ እንዲከናወን የሚረዳ ወሳኝ እርምጃ ነው መሆኑ ተጠቁሟል።
Exit mobile version