አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ህብረተሰቡ በመስቀል በዓል አከባበር ስነ-ስርዓት ላይ ለኮሮና ቫይረስ አጋላጭ ከሆኑ ድርጊቶች እንዲቆጠብ አሳስበዋል፡፡
ሚኒስትሯ እንዳሉትም÷ በተለይ በደመራ ቦታዎች ላይ ርቀትን በመጠበቅ፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ በመጠቀም፣ እጅን በሳሙናና በውሃ በመታጠብ እና ሳኒታይዘር በመጠቀም የበሽታውን ስርጭት የመከላከል ሃላፊነታችንን እንወጣ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አሳስበዋል፡፡
እንዲሁም የመስቀል ደመራ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡