አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኳታር ከአፍጋኒስታን ጋር ስምምነት ላይ የሚገኘው ታሊባን 28 ፖሊሶችን መግደሉ ተሰማ፡፡
ታሊባን ግድያውን የፈጸመው በደቡባዊ አፍጋኒስታን በሚገኝ የፍተሻ ጣቢያ ላይ ነው ተብሏል፡፡
የአገረ ገዢው ቃልአቀባይ ፖሊሶቹ እጅ እንዲሰጡ በታሊባኖች ተጠይቀው ነበር ብለዋል፡፡
ሆኖም ፖሊሶች ፍቃደኛ ባለመሆናቸው በታሊባኖች መገደላቸውን ገልጸዋል፡፡
የታሊባን ቃልአቀባይ የሆኑት ቋሪ ሞሃመድ አህመድ ታሊባን ኃላፊነት እንደሚወስድ ተናግረዋል ፡፡
በሌላ በኩል ሁለቱ ወገኖች በኳታር በሚወያዩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ አጀንዳ ለመምረጥና አካሄዱን ለመወሰን ከሳምንት በላይ መውሰዳቸው ተነግሯል፡፡
አሜሪካና አፍጋኒስታንም ውይይቱ በሚካሄድበት ወቅት ግጭቶች እንዲቀንሱ ጥሪ ቢያቀርቡም ታሊባኖች ቅድመሁኔታዎችን በማስቀመጥ ያለመስማማታቸው ነው የተገለጸው፡፡
ምንጭ፡-አልጀዚራ