አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 8 ሺህ 551 የላብራቶሪ ምርመራ 661 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 71 ሺህ 83 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው ዕለታዊ መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ ባለፈ ባለፉት 24 ሰዓታት የ14 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 141 ደርሷል።
እስካሁን ድረስ 1 ሚሊየን 226 ሺህ 297 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 71 ሺህ 83 ደርሷል።
አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 40 ሺህ 687 ሲሆኑ፥ ከእነዚህም ውስጥ 269 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
እስካሁን በኢትዮጵያ 29 ሺህ 253 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።