አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለ12 ዓመታት በተመሳሳይ ቁጥሮች ሲጫወት የቆየው ሰው የጃክፖት ሎተሪ አሸናፊ መሆኑ ብዙዎችን አስገርሟል።
አሜሪካዊው ዳን ዳምፍ ተመሳሳይ የሎተሪ ቁጥሮችን በመጠቀም ከ 10 ዓመታት በላይ ሲጫወት ቆይቶ የ 50 ሺህ ዶላር አሸናፊ ሆኗል።
የጄፈርሰን ከተማው ዳን ዳምፍ በአውሮፓውያኑ በ 2008 ጀምሮ ላለፉት 12 ዓመታት ተመሳሳይ 10 ቁጥሮችን በመጠቀም ሲጫወት መቆየቱን ተናግሯል።
ባለእድለኛው ሎተሪ ሲያሸንፍ የመጀመሪያው እንዳልሆነ ገልጾ÷ከሁለት ዓመት በፊት 19 ሺህ ዶላር ማሸነፉን አስታውሷል።
የአካባቢው የሎተሪ መስሪያ ቤት ባለሥልጣናትም በተመሳሳይ ቁጥር እንደሚጫወት ነግሯቸው እንደነበር ተናግረው ÷ ጽናቱ ከፍሎታል ብለዋል ።
ዳን ዳምፍ በደረሰው ገንዘብም ያሉበትን እዳ ከከፈለ በኋላ አዳዲስ የእንጨት ሥራ መሣሪያዎችን ለመግዛት ማቀዱን ተናግሯል።
ምንጭ ፡- upi.com