አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ መቐለ 70 እንደርታ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግና ፋሲል ከነማ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እንዲሳተፉ መወሰኑ ተገለፀ።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ በአፍሪካ መድረክ ኢትዮጵያን የሚወክሉት እንዲያሳውቅ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።
ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ የ2011 የፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ እንዲሳተፍ ሲወስን የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ሻምፒዮን ፋሲል ከነማ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እንዲሳተፍ መወሰኑን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽ በኢትዮጵያ መከሰትን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በመቋረጣቸው ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ እና በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚሳትፍ ክለብ እንደማይኖር ተወስኖ እንደነበረ የሚታወስ ነው።