Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ቡና ገበያ ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተጽእኖ መቋቋም መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ቡና ገበያ ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተጽእኖ መቋቋም መቻሉን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ገልጿል።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ የነበራቸው የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳሬክተር እና የግብይት ዘረፍ ሀላፊ አቶ ሻፊ ኦመር ÷የኮሮና ወረርሽኝ በአለም አቀፍ ደረጃ ከተከሰተ ጀምሮ እንደሌሎች የንግድ ዘርፎች የቡናን ገበያ በከፍተኛ ሁኔታ ጎድቶት እንደነበር መረጃዎች ማመላከታቸውን አንስተዋል።

ሆኖም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ቀደም ብሎ ከአርሶ አደሩ እና ከቡና ላኪ ተቋማት ጋር በመነጋገር ስራዎችን በመስራቱ ወረርሽኙ በኢትዮጵያ ሊያሳድር የሚችለውን ተፅዕኖ መቋቋም መቻሉን ገልጸዋል።

ሃላፈው አያይዘውም ከወረርሽኙ ባለፈም የቡና ገበያን ከሚጎዱት ዋነኛው ህገ ወጥ ደላላ እና የኮንትሮበንድ ግብይት መሆኑን ጠቁመው÷ችግሩን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል።

ከዚያም ባለፈ ቡናን በመስኖ እና በክላሰተር በመትከል ወጤት እንደተመዘገበና ወደ ወጭ ገበያ በመላክ ባለፉት 4 ዓመት አመታት የታየውን ስኬት አጠናክሮ ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑንም ነው ያስረዱት።

በዚህም በአሁኑ ወቅት ቡናን በመስኖ እና በክላሰተር እያበቀሉ ያሉ አርሶ አደሮች እና ድርጀቶች ቁጥራቸው እየጨመር መሆኑን ይጠቅሳሉ።

የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣንም የቡናን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እና ያለውን የውጭ ገበያ ፍላጎት ለመጨመር የተለያዩ አሰራሮችን እና እቅዶችን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም ኢትዮጵያ ባለፉት 4 ዓመታት ወደ ውጭ ከላከችው የቡና ምርት ባለፈው ዓመት የተሻለ አፈፃፀም መታየቱን የሚያነሱት አቶ ሻፊ÷በ2012 በጀት ዓመት 270 ሺህ ኩንታል ቡና መላኩን አስረድተዋል።

ከዚያም ባለፈ በ2013 በጀት ዓመትም ጥራቱን የጠበቀ 312 ሺህ ኩንታል ቡና ለመላክ መታቀዱን ተናግረዋል።

ከዚያም ባለፈ ከአርሶ አደሩ ጋር በቅርበት በመነጋገር እና በሀገሪቱ ካሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር እራሱን የቻለ የትምህርት ስርዓት ቀረጾ በመማር ማስተማሩ ላይ ለመግባት እየተሰራ መሆኑንና የቡና ገበያ ሰንሰለቱን ጤናማ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በሲሳይ ጌትነት

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version