የሀገር ውስጥ ዜና

በሶማሌ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ዑመር የተመራ ልዑክ ሰመራ ከተማ ገባ

By Tibebu Kebede

September 22, 2020

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳር አቶ ሙስጠፌ ዑመር የተመራ ልዑክ በአፋር ክልል ዋና ከተማ ሰመራ ገብቷል።

በጉብኝቱ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች የተገኙ ሲሆን ልዑኩ ሰመራ ከተማ ሲገባ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ አቀባበል አድርገውለታል።