አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳር አቶ ሙስጠፌ ዑመር የተመራ ልዑክ በአፋር ክልል ዋና ከተማ ሰመራ ገብቷል።
በጉብኝቱ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች የተገኙ ሲሆን ልዑኩ ሰመራ ከተማ ሲገባ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ አቀባበል አድርገውለታል።
የሶማሌ ክልል ልዑክ በአፋር ሱልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ይገልፃል ተብሏል።
እንዲሁም በአፋር ክልል በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚጎበኝ እና ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው የተነገረው።