አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይናው ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ መስጠት መጀመሩ ተገለፀ።
ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ መስጠት የጀመረበት የመክፈቻ ሥነ ሥርዓትም በቤጂንግ መካሄዱን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሰዲ መረጃ ያመለክታል።
ዩኒቨርሲቲው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በደረሰው የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት አማካኝነት የአማርኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ በቻይና የሚያስተምር ይሆናል።
የምስረታ መርሃ ግብሩ ላይ የቤጂንግ የውጭ ጥናቶች ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ጂያ ውንጂንና በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካይ አቶ ሳሙኤል ፍጹምብርሃን መገኘታቸውንም ኤምባሲው አስታውቋል።