Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ማሊ የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትሯን የሽግግር ጊዜ ፕሬዚዳንት አድርጋ ሾመች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ማሊ የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትሯን ባ ንዳዎን የሀገሪቱ የሽግግር ጊዜ ፕሬዚዳንት አድርጋ ሾመች፡፡

የወታደራዊ መንግስት መሪው ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን ከሀገሪቱ የሚወጡ የዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡

አዲሱ የሽግግር መንግስት ምርጫ ተካሂዶ ህዝባዊ መንግስት እስከሚመሰረት ድረስ ይቆያል ተብሏል፡፡

ከአንድ ወር በፊት የማሊው ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬዬታ  በሀገሪቱ ወታደሮች በቁጥጥር ስር ውለው

ስልጣን መልቀቃቸውን በመግለፅ ፓርላማው መበተናቸው የሚታወስ ነው፡፡

ይህንንም ተከትሎ ወታደራዊ መንግስቱ ሀገሪቷን ሲመራት ቆይቷል፡፡

ሆኖም ከአፍሪካ ህብረት፣ ከቀጠናው አገራት ከተባበሩት መንግስታትና ከተለያዩ ወገኖች ውግዘት ሲቀርብበት ሰንብቷል፡፡

ባለፈው ሳምንትም የቀጠናው አገራት ጊዜያዊው ፕሬዚዳንት ከህዝቡ በኩል እንዲመረጥ አጽንዖት ሰጥተው ማሳሰባቸው ነው የተነገረው፡፡

አሁን ይፋ በሆነው ውጤትም ወታደራዊ መንገስቱ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት መምረጡ ተገልጿል፡፡

 

ምንጭ፡-አልጀዚራ

Exit mobile version