አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብሪታኒያ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከባድ የሆነ ሁኔታ ውስጥ እንደሆነች ተሰማ።
ሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ረገድ ከባድ ሁኔታ ውስጥ ናት ሲሉ የመንግስት ዋና የህክምና አማካሪ ተናግረዋል።
ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ እየሄደች ነው ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
እርምጃ ካልተወሰደ በቀርም እስከሚቀጥለው ወር መጨረሻ ድረስ በየቀኑ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ ሊያዙ ይችላሉ ብለዋል።
በቫይረሱ የሚያዙ እና በቫይረሱ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ለመቀነስም ተጨማሪ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
መንግሥት ተጨማሪ ገደቦችን ከግምት ውስጥ በማስገባት አገሪቱ ከባድ የሆነ ሁኔታ እየገጠማት በመሆኑም አስጠንቅቀዋል።
ነገር ግን ሁሉም ሰው ህጎቹን የሚከተል ከሆነ ገደቦችን ማስቀረት እንችላለን ብለዋል።
አሁን ላይ በሀገሪቱ 394 ሺህ 257 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 41 ሺህ 777 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ