አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከሰሞኑ አንድ ሩሲያዊ ወጣት በእድሜው ምክንያት አነጋጋሪ ሆኗል።
ነገሩ እንዲህ ነው፤ ዴኒስ ቫሹሪን የተባለው ወጣት በልደት የምስክር ወረቀቱ መሰረት የተወለደው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1987 ሲሆን፥ በዚህም አሁን የ32 ዓመት ወጣት ነው።
ይሁን እንጂ እሱ ገና በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ያለ ነው የሚመስለው ተብሏል።
በዚህም ስለ እድሜው በአንድ የዩቲዩብ ቻናል ላይ ቀርቦ ቃለ ምልልስ ጋደረገ በኋላ በሩሲያ አነጋጋሪ መሆን ችሏል።
የ32 ዓመቱ ወጣት ሁልጊዜም ቢሆን በእድሜው በኩል ከሰዎች እምነትን እንደማያገኝ ይናገራል፡፡
ለዚህም ነው ከተማ ከመኖር ይልቅ ክራስኖያርስክ በምትባል የሩሲያ ክልል በትንሽ መንደር ውስጥ መኖርን የሚመርጠው ተብሏል፡፡
በአካባቢው ሁሉም ሰው ስለሚያውቀው ጊዜውን በአደን፣ ዓሳ በማጥመድ እና ከሴት ጓደኛው ጋር በመሆን ያሳልፋል።
በዚህ በሚኖርበት አከባቢ የሚገኙ ጓደኞቹ አያቴ በማለት ሲጠሩት ይደመጣል ነው የተባለው።
ገና በልጅነት እንደሌሎች ልጆች እንዳልሆነ ያስተዋሉት ቤተሰቦቹ እሱ ከእድሜ እኩዮቹ ውስጥ ሁልጊዜ ትንሹ ነበር ይላሉ።
ዴኒስ ከአሁን በኋላ በአካል መለወጥ እንደማልችል ስገነዘብ መጀመሪያ ላይ በተወሰነ ደረጃ የመረበሽ ስሜት ተሰማኝ” ብሏል።
ሁሉም ነገር እንዴት እንደሚሆን፣ ሕይወቴ እንዴት እንደሚቀጥል፣ ለእኔ ከባድ ቢሆንብኝ ብዬ አሰብኩ ያለው ወጣቱ አሁን ላይ መደበኛ ሕይወትን መምራት ቢችልም አንዳንድ ጊዜ እውነተኛ ዕድሜውን መግለፅ እና ማረጋገጥ እንዳለበት ያምናል ነው የተባለው ዴኒስ፡።
ይህ እንዳለ ሁኖ ስለ ሁሌታውም እስካሁን ዶክተር እንዳላማከረ ነው የተገለፀው፡፡
ምንጭ፦ ኦዲቲ ሴንተራል