አዲስ አበባ፣ መስከረም 11 ፣ 2013(ኤፍ.ቢ.ሲ)ከ25 ሚሊየን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ በቢሾፍቱ ከተማ የተገነባው ባለ 400/230/15 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታወቀ።
የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ገብረ እግዚአብሄር እንደገለፁት የማከፋፈያ ጣቢያው የግንባታ፣ የፍተሻ እና የሙከራ ስራ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል፡፡