አዲስ አበባ፣ መስከረም 10 ፣ 2013(ኤፍ.ቢ.ሲ)በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ከተማ እና ቢሻን ጉራቻ ከተማ ፓሊስ እንዲሁም ለኦሮሚያ ልዩ ሀይል አባላት የተለያየ ማዕረግ ተሰጥቷል ።
ለፀጥታ አባላቱ የተሰጠው ማዕረግ ከረዳት ሳጅን እስከ ረዳት ኮምሽነር ድረስ መሆኑ ተመላክቷል ።
ዛሬ በነበረው ስነ ስርዓት የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናትና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የፀጥታው ዘርፍ አመራሮች ተገኝተዋል።
የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ሙስጠፉ ከድር ÷ ማዕረጉ ከሁለት እስከ አራት አመት በፀጥታው ዘርፍ ተሰማርተው ጥሩ የሚባል ውጤት ያስመዘገቡና በተሻለ ስነ ምግባር ሀላፊነታቸውን ለተወጡ አባላት የተሰጠ ነው ብለዋል።
በክልሉ ፓሊስ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ባስመዘገቡት ውጤትና በነበራቸው አገልግሎት የተሰጠው ማዕረግ አባላቱ ጠናክረው እንዲሰሩና የስራ ተነሳሽነታቸው እንዲጨምር ያግዛልም ሲሉ ገልጸዋል።
በሀይለየሱስ ስዩም
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።