አዲስ አበባ፣ መስከረም 10 ፣ 2013(ኤፍ.ቢ.ሲ)የሀዲያ ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” ክብረ በዓል በሀዲያ ዞን እየተከበረ መሆኑን የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ አስታውቋል።
የዘመን መለወጫ በዓሉ የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች እና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተለያዩ ክንዋኔዎች በመከበር ላይ መሆኑን ከዞኑ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።