አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “በድህረ ኮቪድ-19 የምንሰራውን ሁሉ የአየር ንብረት ለውጥን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲሆን ማድረግ ነው አሉ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ።
የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘዉዴ የግሎባል ሴንተር ኦን አዳፕቴሽን የአፍሪካ ቢሮ ምረቃ ሥነ ሥርዐት ላይ ንግግር አድርገዋል።
ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ በንግግራቸውም የአየር ንብረት ለውጥን ያማከሉ ፖሊሲዎችን መቅረጽ ያለዉን ጠቀሜታ ማብራራታቸውን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
በዚህም “በድህረ ኮቪድ-19 ዓላማችን መሆን ያለበት እንደገና መነሳትና ማገገም ብቻ ሳይሆን የምንሰራውን ሁሉ የአየር ንብረት ለውጥን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲሆን ማድረግ ነው” ብለዋል።
“የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና ለመላመድ እንዲሁም የፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ግቦችን ለማሳካት ጥረታችንን እንደገና ማደስ ይኖርብናል፤ ጊዜ የለንም” ሲሉም ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ተናግረዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።