Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በካዛንቺስ የፅዳት ዘመቻ አከናወኑ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የኢፌዴሪ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በካዛንቺስ የፅዳት ዘመቻ አከናወኑ።

ጠቅላይ ሚኒስትርሩ የፅዳት ዘመቻውን ያከናወኑት ከከተማዋ ባለታክሲ ባለንብረቶች ጋር በመሆን ነው።

በፅዳት ዘመቻው 13 የሚነባስ ታክሲ እና 3 የሀይገር ሚድባስ ማህበራት ተሳትፈዋል።

የዘመቻውም ዓላማ “ተርሚናሎቻችን ከፀዱ ከመተላለፊያነት ወደ ማረፊያነት ይቀየራሉ”  የሚል መሆኑ ነው የተመለከተው።

የታክሲ ማህበራቱ ባለፈው ሳምንት ባካሄዱት ስብሰባ በመዲናዋ ለአዛውንቶች፣ ለአቅመ ደካማዎች እና ለህሙማን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መርሃ ግብር ይፋ ማድረጋቸው የታወሳል።

 

 

በአልአዛር ታደለ

Exit mobile version