Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የቀድሞው ፕሬዚዳንት ላሚን ዲያክ አራት ዓመት ተፈረደባቸው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የቀድሞ ፕሬዚዳንት ላሚን ዲያክ በሙስና ጥፋተኛ ተብለው አራት ዓመት ተፈረደባቸው፡፡

የ87 ዓመቱ ላሚን ዲያክ ከሙስና በተጨማሪ በህገውጥ የገንዘብ ዝውውር ተጠያቂ ተደርገዋል፡፡

በአውሮፓውያኑ 2012 የለንደን ኦሊምፒክ መካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡

በዘህ ውድድር ላይ አበረታች መድሐኒት የተጠረጠሩ ሩስያውያንን የምርመራ ውጤት ይፋ ባለማድረግ እና ውድድራቸውን እንዲቀጥሉ በመወሰናቸው ነው ወንጀለኛ የተባሉት፡፡

ላሚን ዲያክ አበረታች መድሐኒቱን ውጤት ይፋ ባለማድረጋቸው 3 ሚሊየን ዩሮ መቀበላቸውም ተሰምቷል፡፡

ጠበቃቸው በበኩሉ ውሳኔው ሰብዓዊነት የጎደለውና ተመጣጣኝነት የሌለው ነው በማለት ይግባኝ እንደሚጠይቅ ተናግሯል፡፡

ችሎቱ ላይ የተሰየሙት ዳኛ የላሚን ዲያክ ስራ አትሌቲክሱንና አበረታች መድሐኒትን ለመዋጋት የሚደረገውን ጥረት የሚጎዳ ነው ብለዋል፡፡

ላሚን ዲያክ ከአውሮፓውያኑ 2015 ጀምሮ በቤት ውስጥ እስር ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ

Exit mobile version