Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

“የልማት አርበኞች” በሚል ርእስ በአቶ አባዱላ ገመዳ የተፃፈው መጽሃፍ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “የልማት አርበኞች” በሚል ርእስ በአቶ አባዱላ ገመዳ የተፃፈው መጽሃፍ በዛሬው እለት ተመረቀ።

መፅሃፉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል መንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው እለት ተመርቋል።

“የልማት አርበኞች” የሚል ርእስ ያለው መፅሃፉ አቶ አባዱላ ገመዳ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግት ርእሰ መስተዳድር በነበሩበት ወቅት በክልሉ በተሰሩ የልማት ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑም ተነግሯል።

በተመሳሳይ በመፅሃፍ ምርቃቱ ወቅት በክልሉ ልማት ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

በዚህም ባለፉት ዓመታት በክልሉ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ልምድ እና እስካሁኑ ጊዜ ያለው የልማት እንቅስቃሴ በመድረኩ ላይ ቀርቧል።

Exit mobile version