አዲስ አበባ ፣ መስከረም 7 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሱዳን አሞኒየም ናይትሬትን ጨምሮ ብዛት ያለው ተቀጣጣይ የፈንጂ ቁሶችን መያዛቸው የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘም 41 ተጠርጣሪዎች መታሰራቸውን ገልጸዋል።
የተያዘው አሞኒየም ናይትሬት ባለፈው ወር በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት የፈነዳው ኬሚካል አይነት መሆኑም ተመላክቷል።
በመሆኑም አሁን የተያዘው አሞኒየም ናይትሬትና ተቀጣጣይ የፈንጂ ቁስ መጠን ዋና ከተማዋ ካርቱም ን ለማጥፋት በቂ እንደነበር የሀገሪቱ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታውቋል።
የፀጥታ ኃይሉ ቃል አቀባይ በበኩላቸው÷ ተቃዋሚዎች በሱዳን የሽግግር መንግሥት ላይ የጥፋት ዘመቻ እያዘጋጁ ይሆናል የሚል ስጋት መኖሩን ተናግረዋል።
ነገር ግን ማስረጃ የሚሆን ነገር አለማቅረባቸው ተገልጿል።
ምንጭ፡-ቢቢሲ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።