አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ30 ሚሊየን አለፈ፡፡
በአለም ዙሪያ እስካሁን 30 ሚሊየን 42 ሺህ 218 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ነው የተገለጸው፡፡
ወደ አንድ ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎችም በቫይረሱ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
እስካሁን ባለው መረጃ 945 ሺህ 159 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይዎታቸው ሲያልፍ 21 ሚሊየን 808 ሺህ 302 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡
በአለም በከፍተኛ ሁኔታ ቫይረሱ ከጸናባቸው አገራት ቅድሚያ የምትይዘው አሜሪካ 6 ሚሊየን 828 ሺህ በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ ሲያዙ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
በተጨማሪም በቅርቡ ቫይረሱ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ካለባቸው አገራት ሁለተኛ የተቀመጠችው ህንድ በቫይረሱ የተያዙባት ዜጎቿ ቁጥር 5 ሚሊየንን ሲሻገር ከ83 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
በዚህም በአለም አቀፍ ደረጃ ከአሜሪካ እና ህንድ ቀጥሎ ብራዚል፣ ሩሲያ እና ፔሩ ወረርሽኙ የበረታባቸው አገራት በመሆን እስከ አምስተኛ ደረጃን እንደያዙ ነው፡፡
ምንጭ፡- ወርልድ ኦ ሜትር