አዲስ አበባ፡ መስከረም 6 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የስራ ዘመናቸዉን ያጠናቀቁ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን አሰናብተዋል።
ፕሬዚዳንቷ ያሰናበቷቸው የስራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ የስዊዘርላንድ ፣ የኢራን እና የቻይና አምባሳደሮችን መሆኑ ተገልጿል።
በዚሁ ወቅት አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ በቆዩበት ጊዜ ሁሉ ለተደረገላቸዉ ትብብር ማመስገናቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል ።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።