አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ እድገት ለመደገፍ እና በአነስተኛ መሬት ለሚያርሱ ገበሬዎች የተሻለ አማራጭን ለመፍጠር 80 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አደረገ።
የአለም ባንክ ስራ አስፈፃሚ ቦርድ የባንኩ አንድ አካል የሆነው አለም አቀፉ የልማት ማህበር ለኢትዮጵያ 80 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንዲያደረግ በትናትናው ዕለት ውሳኔ አሳልፏል።