የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ውይይት እያካሄዱ ነው

By Tibebu Kebede

December 21, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ዛሬ በሱዳን ካርቱም የሶስትዮሽ ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡

የሶስቱ ሀገራት ውሃ ሚኒስትሮች በካርቱም በግድቡ ውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ዙሪያ ትኩረት በማድረግ እንደሚወያዩ ተነግሯል፡፡

ይህ ውይይቱ በአለም ባንክ እና አሜሪካ ታዛቢነት ከሚካሄዱት አራት ስብሰባዎች ሶስተኛው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ውይይት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ፣ ካይሮ እንዲሁም በዋሽንግተን መካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡