አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2012(ኤፍቢሲ) አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ የከተማ አስተዳደሩ ለጀመረው የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር በመልካም ወጣት ፕሮጀክት ስም 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ኢንጅነር ታከለ ኡማ እና የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በተገኙበት አስረክቧል፡፡
የመልካም ወጣት ፕሮጀክት የከተማ አስተዳደሩ የጀመረውን የህጻናት ምገባ በመደገፍ ለሚቀጥሉት አምስት አመታት በጠቅላላው የ 50 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንደሚያደርግም አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ተናግሯል፡፡
ኢንጅነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ለተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ላደረገው ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ህግ እና ተቋማዊ ይዘት እንዲኖረው እና በዘላቂነት እንዲተገበር መወሰኑና የተማሪዎች የምገባ ኤጀንሲ መቋቋሙም ይታወሳል፡፡