Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ኑሮአቸውን በጎዳና ላይ ላደረጉ ዜጎች ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ከአዲስ አበባ ካቶሊካዊይት ሰበካ ሐዋሪያዊ ጽህፈት ቤት እና የቦስኮ ልጆች ድራማ ቡድን ጋር በመተባበር ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ወገኖችን ማዕድ አጋርተዋል።

ጎዳና ተዳዳሪዎቹን ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪው አቶ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎች የከተማ አስተዳዳሩ ከፍተኛ አመራሮች መግበዋል ።

በጊዜያዊነት በጎዳና ላይ የወደቁት ወገች ብዙ ህልምና አቅም እንዳላቸው ተረድቶ ለእነርሱም አዲስ የተስፋ ብርሃን እንዲወጣላቸው እና ህይወታቸው በዘላቂነት እንዲቀየር ሁላችንም ትኩረት ሰጥተን፣ ተባብረንና ተቀናጅተን መስራት አለብን ብለዋል ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ።

ሁሉም የከተማዋ ማህበረሰብ የመደጋገፍ እና የመረዳዳት ባህሉን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም መግለፃቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የማዕድ ማጋራቱን ለደገፉት እና ላስተባበሩት የአዲስ አበባ ካቶሊካዊይት ሰበካ ሐዋሪያዊ ጽህፈት ቤት እና የቦስኮ ልጆች ድራማ ቡድንን በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል ።

Exit mobile version