አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የመረጃ፣ የደህንነትና የፀጥታ ተቋማት የኢኮኖሚ ወንጀሎችን፣ ሽብርተኝነትንና ህገ ወጥ ድርጊቶችን በጋራ ለመከላከልና ለመቆጣጠርተስማምተዋል።
በዚህም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እንዲሁም የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ እና የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል በአገሪቱ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ የአምስትዮሽ ትብብራቸውን አጠናክረው ለመሥራት ተስማምተዋል፡፡