የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ለአረጋውያን፣ ለጎዳና ተዳዳሪዎችና ለችግር ለተጋለጡ አካል ጉዳተኞች የምሳ ግብዣ አደረጉ

By Tibebu Kebede

September 11, 2020

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለአረጋውያን፣ ለጎዳና ተዳዳሪዎች እና ለችግር ለተጋለጡ አካል ጉዳተኞች የምሳ ግብዣ አድርገዋል።

አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በተደረገው የምሳ ግብዣው ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ተጋባዦቹን አስተናግደዋቸዋል።

በሸገር ፓርክ ወዳጅነት አደባባይ በተደረገው የምሳ ግብዣው ላይም 500 አረጋውያን፣ ጎዳና ተዳዳሪዎች እና ችግር ለተጋለጡ አካል ጉዳተኞች ተገኝተዋል።

በተያያዘ ዜና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዴቦራ ፋውንዴሽንን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይም ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውም ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ጉብኝቱን አስመልክቶ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ “ዴቦራ ፋውንዴሽን የአእምሮ ሕመም የገጠማቸውን ወጣቶች ሕይወት ለመለወጥ የሚሠራው ሥራ የሚደነቅ ነው” ብለዋል።

“ዛሬ ጠዋት ወጣቶቹን ለመጎብኘት እና መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንላቸው ለመመኘት በመካከላቸው ተገኝቼ ፋውንዴሽኑ የሚሠራውን አድንቄአለሁ” ሲሉም አስታውቀዋል።

በአላዛር ታደለ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።