Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአፍሪካ ልማት ባንክ ኮሮናን ለመከላከል 27 ነጥበ 3 ሚሊየን ዶላር አፀደቀ

FILE PHOTO: The headquarters of the African Development Bank (AfDB) are pictured in Abidjan, Ivory Coast, September 16, 2016. Picture taken September 16, 2016. REUTERS/Luc Gnago/File Photo - RC196B9DEF90

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ ልማት ባንክ በአህጉሪቱ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው እንቅስቃሴ 27 ነጥብ 3 የአሜሪካ ዶላር ማጽደቁን አስታውቋል።

ይህ የፋይናንስ ድጋፍ በኮቪድ 19 ላይ የተቀናጀ አፍሪካዊ ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ አቅም እንደሚሰጥ ነው የተገለጸው።

በዋናነትም በወረርሽኙ ምክንያት የደረሰውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽህኖ ለመቋቋም ያግዛልም ነው የተባለው።

በተጨማሪም ድጋፉ የአፍሪካን የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከላትን በመደገፍ በአፍሪካ ልማት ፈንድ በኩል ድጋፉ ለሚያስፈልጋቸው አገራት ቴክኒካዊ እገዛ እንደሚያደርግ ተነግሯል።

በልማት ባንኩ የሚደረጉ ድጋፎች በአፍሪካ አገራት የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመከላከል በአየር በባህርና በመሬትና ለሚከናወነው ተግባራት ያለግላሉ መባሉን ኒው ታይምስን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version