Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባለፉት 24 ሰዓታት 878 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ8 ሰዎች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 16 ሺህ 665 የላብራቶሪ ምርመራ 878 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 62 ሺህ 578 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

በ24 ሰዓታት ውስጥ የ8 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 974 ደርሷል።

በትናንትናው ዕለት 586 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 23 ሺህ 640  መድረሱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

እንዲሁም 330 ፅኑ ህሙማን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

እስከአሁን በኢትዮጵያ 1 ሚሊየን  110 ሺህ 495 የላብራቶሪ ምርመራ እንደተደረገ መረጃው ያሳያል ።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version