Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአለም በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ900 ሺህ ተሻገረ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በአለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ900 ሺህ በልጧል፡፡

እንደ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ÷በወረርሽኙ ምክንያት ከ908 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

ከዚያም ባለፈ ከ 28 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መረጃው ያሳያል ።

ሆኖም ከ20 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎችም ከቫይረሱ ማገገማቸውም ተገልጿል፡፡

በአለም ላይ አሜሪካ፣ ህንድ፣ ብራዚል፣ ሩሲያ እና ፔሩ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከበረታባቸው ሀገራት መካከል ከ አንድ እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

ምንጭ፡- ሲ.ጂ.ቲ.ኤን እና ዎርልድ ኦ ሜትር

Exit mobile version