የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ተመድ 7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር የዘላቂ ልማት ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራረሙ

By Abrham Fekede

September 10, 2020

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር የዘላቂ ልማት ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራረሙ።

ማዕቀፉ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን ከአውሮፓውያን 2020 እስከ 2025 የሚተገበር መሆኑ ተነግሯል፡፡