Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ህክምና ለሚከታታሉ ዜጎች ወጪያቸው በመንግስት ይሸፈናል-ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2013 ዓ.ም መንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ህክምና ለሚከታታሉ ዜጎች አመቱን ሙሉ የህክምና ወጪያቸው በመንግስት የሚሸፈን መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ምክትል ከንቲባዋ የምስጋና ቀንን ምክንያት በማድረግ የዘውድቱ ሆስፒታል ለይቶ ማቆያን ጎብኝተዋል።

በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ህከምና ለሚከታታሉ ዜጎች አመቱን ሙሉ የህክምና ወጪያቸው በመንግስት የሚሸፈን መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባዋ ገልጸዋል።

ህሙማኑ በሳምንት ሶስት ጊዜ የኩላሊት እጥበት በማድረግ ለከፍተኛ ወጭ እየተዳረጉ መሆኑ ይታወቃል።

ስለሆነም መንግስት ችግሩን ተረድቶ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚያደርግ መሆኑን ወይዘሮ አዳነች ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በሶስት የመንግስት ሆስፒታሎች ማለትም በሚኒሊክ፣ ዘውዲቱና ጳውሎስ ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል።

በእነዚህ ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት እያደረጉ ላሉ ዜጎች በ2013 ዓ.ም አመቱን ሙሉ ወጪያቸው እንደሚሸፈን ምክት ከንቲባዋ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version