የሀገር ውስጥ ዜና

አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ 551 ለሚሆኑ የፌዴራል ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ

By Tibebu Kebede

September 09, 2020

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2013 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በፌዴራል፣ በክልልና በመከላከያ ወታደራዊ ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ የፌዴራል ታራሚዎች በተለያዩ መስፈርቶች መነሻ ለ551 ታራሚዎ ይቅርታ ተደረገ ።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የይቅርታና ምህረት ቦርድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘለቀ ዳላሎ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት፥ በፌዴራል ማራሚያ ቤቶች፣ በመከላከያ ወታደራዊ ማረሚያ ቤት እና በተለያዩ ክልሎች ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ የፌዴራል ታራሚዎች የይቅርታ ቦርድ ያቀረበውን ማስረጃ መርምሮ ይቅርታ እንዲደረግላቸው ለኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባቀረበው የውሳኔ ሀሳብ መሰረት ፕሬዚዳንቷ የውሳኔ ሀሳቡን ተቀብለው በማጽደቅ ታራሚዎቹ የይቅርታው ታጠቃሚ ሆነዋል፡፡