A volunteer removes water from a flooded Health center after heavy rains in Guediawaye on the outskirts of Dakar, Senegal September 6, 2020.REUTERS/ Zohra Bensemra

ፋና ስብስብ

ሴኔጋል በ3 ወር ውስጥ የምታገኘውን የዝናብ መጠን በ7 ሰዓት ውስጥ ብቻ አገኘች

By Feven Bishaw

September 07, 2020

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሴኔጋል በ3 ወር ውስጥ የሚዘንበው የዝናብ መጠን በ7 ሰዓት ውስጥ ብቻ መዝነብ ችሏል።

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ሴኔጋል በሶስት ወር ውስጥ የሚዘንበውን የዝናብ መጠን በ7 ሰዓት ውስጥ ማግኘቷን የሃገሪቱ የውሃ ሚኒስቴር በሃገሪቱ ብሄራዊ የቴሌቪዥ ጣቢያ ቀርበው አስታውቋል።

የዝናቡ መጠንም 124 ሚሊሜትር ሆኖ ተመዝግቧል ነው የተባለው።

ይህ ከሐምሌ እስከ መስከረም ባለው አጠቃላይ የዝናብ ወቅት የምናገኘው ድምር ዝናብ ነው ሲሉም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የሃገሪቱ መንግስትም ይህ ከታወቀ በኋላ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ዕቅዱን ይፋ አድርጓል።

ዝናቡ ባስከተለው ጎርፍም የ3 ህፃናት ህይወት ማለፉ ታውቋል።

ባለፈው ሳምንት በኒጀር፣ ናይጄሪያ፣ ቻድ እና ካሜሮንን ጨምሮ በምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ሳህል አካባቢዎች ከባድ ዝናብ የተመዘገበ ሲሆን በዚህም በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ለህልፈት ሲዳርግ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ