Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአስራት ሚዲያ ጋዜጠኞች እና የካሜራ ባለሙያዎች ዋስትና ተፈቀደላቸው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአስራት ሚዲያ ጋዜጠኛ፣ የካሜራ ባለሙያ እና ኤዲተር የሆኑ አራት ባለሙያዎች ዋስትና ተፈቀደላቸው።

በሚዲያ ሁከትና አመጽ ቀስቅሰዋል ተብለው ተጠርጥረው የፍርድ ሂደታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።

ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ የተቀበለው ፍርድ ቤቱም እያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፈቅዷል።

በታሪክ አዱኛ

Exit mobile version