Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ህንድ 118 ተጨማሪ የቻይና መተግበሪያዎችን አገደች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህንድ 118 ተጨማሪ የቻይና መተግበሪያዎችን አገደች።

እገዳው የተጣለውም በህንድ እና በቻይና መካከል ያለው የድንበር ውዝግብ እየተባባሰ በመምጣቱ መሆኑ ታውቋል።

በዚህም ሃገሪቱ የህንድን ሉዓላዊነት እና ታማኝነትን የሚነካ ነው በሚል 118 የቻናይ መተግበሪያዎችን አግዳለች ነው የተባለው።

የሕንድ የኤሌክትሮኒክስ እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው መተግበሪያዎቹ በቻይና የበይነመረብ ግዙፉ ቴንሴንት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ያራምዳሉ።

ህንድ እና ቻይና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሁለቱ ሃገራት ድንበር በሆነችው ሂማሊያ ግጭቶች መፈጠሩ ይታወሳል፡፡

በዚህም 20 የህንድ ወታደሮች እና በቻይና በኩልም መጠኑ ያልተገለፀ ጉዳት ደርሷል፡፡

ይህን ተከትሎም ህንድ አጭር ምስል ማጋሪያ የሆነውን ቲክቶክን ጨምሮ 59 የቻይና መተግበሪያዎችን አግዳለች፡፡

አሁን ላይ የተዘጉት ሌሎች መተግበሪያዎች ጨዋታዎችን ወይም ጌሞችን፣ ኦንላይን ክፍያ አገልግሎቶችን የራስ ፎቶዎችን ለማስተካከል የሚረዱ ሶፍትዌሮችን ጭምር ያጠቃልላሉ፡፡

በዚህም መተግበሪዎች በህንድ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተጠቃሚዎች አሏቸው ነው የተባለው፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

Exit mobile version