Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኬንያ አልሻባብን ይደግፋሉ ያለቻቸው የ9 ሰዎችን ንብረት አገደች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኬንያ አልሻባብን ይደግፋሉ ያለቻቸው የዘጠኝ ሰዎችን ንብረት አገደች።
 
የኬንያ የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ እንዳስታወቁት፥ ውሳኔው በአገር ውስጥ የሚከሰተውን ሽብር ለመከላከል ያለመ ነው ብለዋል።
 
የአገር ውስጥ የደህንነት ሚኒስትሩ ከአሁን በኋላ በኬንያ ድንበር ውስጥ ለአልሻባብ ድጋፍ አያደርጉም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
 
የአልሻባብ ቡድን አጀንዳውን ለማሳካት ሰዎችን እየመለመለ እንደሚገኝም አስጠንቅቀዋል፡፡
 
ይህ የሚኒስትሩ መግለጫ የተሰማው ሰሞኑን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኮሮና ቫይረስ ተፅዕኖ እና በጸጥታ ጉዳይ በቨርቹዋል ከዓለም አቀፍ ተቋማትና ሀገራት መሪዎች ጋር መምከራቸውን ተከትሎ ነው፡፡
 
ፕሬዚዳንት ኡሁሩ በውይይታቸው ወረርሽኙ ለአሸባሪዎች ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
 
ኬንያ ከዚህ ቀደም የአልሻባብ ጥቃት የደረሰባት ሲሆን÷ ከአውሮፓውያኑ 2011 ጀምሮ ወታደሮቿን በሶማልያ ማሰማራቷ ይታወቃል፡፡
 
ምንጭ፦ ቢቢሲ
Exit mobile version