አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአንድ ሀገር ብልጽግና ከማኅበራዊ ኃላፊነት መጎልበት ጋር ከፍተኛ ትሥሥር እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፥ “ማኅበራዊ ኃላፊነት ዝቅተኛ የሆነባቸው ሀገራት ለዕድገት ብዙ ማገዶ ይጨርሳሉ” ብለዋል።
“የመሠልጠን ጉዟቸውም መሰናክል የሚገጥመው በዋናነት ኃላፊነት ከማይሰማቸው ዜጎቻቸው ነው” ሲሉም ገልፀዋል።
ዜጎቻችን ማኅበራዊ ኃላፊነት እንዲሰማቸው አርአያ የሚሆኑ ሰዎች ከፊት ከቀደሙ የብልጽግና መንገዱ ቀና ይሆናል ያሉ ሲሆን፥ “አርአያነቱም ከንግግር በዘለለ በተግባር ሲገለጥ የምናስበውን ውጤት በፍጥነት ማሳካት እንችላለን” ሲሉም አስታውቅዋል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።