Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች 12 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት በእሳት አደጋ የወደመባቸውን ተጎጂዎች ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 27 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲ.ኤም.ሲ አሊታድ ሚካኤል በደረሰው የእሳት አደጋ ተጎጂ የሆኑ ግለሰቦችን አጽናንተዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ከ6 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ጀምሮ በተከሰተው የእሳት አዳጋ 12 ሚሊየን ብር የሚገመት 18 የንግድ ሱቆች ፣11 መጋዘኖች እና አንድ ባርና ሬስቶራንት ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጉዳት በደረሰበት አካባቢ በመገነኘት በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት ከባድ ቢሆንም በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት ባለመድረሱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው የከተማ አስተዳደሩ በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋም አስፋላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ የእሳት አደጋው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ መከላከል ሰራተኞች፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የአካባቢው ማህበረሰብ በመተባባር አደጋውን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን መግለፃቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

48 ሚሊየን የሚሆን ንብረት ደግሞ ከእሳት አደጋው ለማዳን መቻሉ የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version