አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 27 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪ በሁለቱም የነዳጅ ታንከሮቹ ውስጥ ግምታዊ ዋጋቸው 5 ሚሊየን ብር የሆኑ 23 ሺህ 750 ስቴካ ሻምላን ሲጋራ እና 863 ስቴካ ሺሻ ይዞ ሲጓዝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው አስታወቁ።
መነሻውን ምዕራብ ሐረርጌ ዞን፣ ሚኤሶ ወረዳ አሰቦት ያደረው ነዳጅ ጫኝ ተሸከርካሪ በሁለቱም የነዳጅ ታንከሮቹ ውስጥ ስቴካ ሻምላን ሲጋራ እና ስቴካ ሺሻውን ጭኖ ወደ ሚሌ መስመር በመጓዝ ላይ እያለ አዋሽ አርባ ላይ በፌዴራል ፖሊስና በጉምሩክ መረጃ ሰራተኞች ተይዟል።