Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፌስቡክ እና ትዊተር ሩሲያ ለምትፈፅመው የምርጫና ሌሎች ጣልቃ ገብነት የተፈጠሩ ናቸው ያሏቸውን ገፆች ዘጉ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 27 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ፌስቡክ እና ትዊተር ሩሲያ ለምትፈፅመው የምርጫና ሌሎች ጣልቃ ገብነት የተፈጠሩ ናቸው ያሏቸውን ገፆች መዝጋታቸውን አስታወቁ።

ዘመቻው ለሩስያ መንግስት ቅርብ ከሆነውና በአውሮፓውያኑ 2016 በአሜሪካ ምርጫ ጣልቃ ገብቷል ተብሎ ከሚከሰሰው የሩስያ የበይነ መረብ ምርምር ኤጀንሲ (አይ አር ኤ) ጋር የተያያዘ መሆኑም ተመላክቷል።

ከዚያም ባለፈ ሁለት ወር የቀረው ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ጆ ባይደን የሚፋለሙበት አሜሪካ ምርጫ ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተሰምቷል ነው የተባለው።

በዚህም ፌስቡክ አነስተኛ የትስስር መረብ ያላቸውንና የሩስያ እጅ አለበት ያላቸውን አካውንቶችና ገጾች መዝጋቱን አስታውቋል።

ፌስቡክ በዘመቻው የዘጋቸው 13 አካውንቶች፣ ሁለት ገጾችትኩረታቸው በአሜሪካ የሚደረጉ ህዝባዊ ውይይቶች ላይ ነበርም ሲል ገልጿል።

ትዊተርም በበኩሉ ከዚሁ ድርጅት ጋር ግንኙነት ያላቸው አምስት አካውንቶችን መዝጋቱን አስታውቋል ።

ድርጅቱ ስራውን ያከናውን የነበረው ለትርፍ ባልተቋቋመ ድርጅት ስም ተመዝግቦ በእንግሊዘኛ እና በአረብኛ የሚነበብ ድረ ገጽ ያለው መሆኑ ተነግሯል።

ነገር ግን ዘመቻው በጣም ውስን ስኬት ማስመዝገቡን ፌስቡክ እና ትዊተር ተናግረዋል ።

ፌስቡክና ትዊትር ከኤፍ.ቢ.አይ ጋር አብረው ከሩስያ ጋር ንክኪ ያለውን ፒስዳታ የተሰኘ ድረገጽ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ግብረ ኃይል አቋቁመው ሲሰሩ ነበርም ነው የተባለው ።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version