ዓለምአቀፋዊ ዜና

የቱኒዚያ ፓርላማ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመውን ምሁራንን ያካተተውን አዲስ መንግስት አፀደቀ

By Meseret Awoke

September 02, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 27፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የቱኒዚያ ፓርላማ በጠቅላይ ሚኒስትር ሂቼም መቺቺ የተቋቋመውን ምሁራንን ያካተተውን አዲስ መንግስት አፀደቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ በፊት እንደነበረው ከፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት በተቃራኒ በመንግስታቸው ውስጥ ባለሙያዎችን አካተዋል ፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች መጀመሪያ በባለሙያዎች ምርጫ ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን፥ የፓርላማ አባላቱ 134 በ67 በሆነ ድምጽ አዲሱን መንግስት አባላት ሹመት በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር አዲሱ መንግስት በፖለቲካ አለመረጋጋት ወቅት ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮችን መፍታት ላይ እንደሚያተኩር ተናግረዋል ፡፡

ባለፈው ዓመት ከተካሄደው የፓርላማ አባላት ምርጫ በኋላ ይህ የቱኒዚያ ሦስተኛ መንግሥት ነው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ