አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 26፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት 70 ሺህ ሕፃናት የተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት ከፍተኛ የሆነ በረሃብ የመሞት አደጋ ተጋርጦባቸዋል ሲል የህጻናት አድን ድርጅት አስጠንቅቋል ፡፡
ኮሮና መከሰቱን ተከትሎ የተጣሉ እገዳወች እና እርምጃዎች በሀገራቱ የሚገኙ ቤተሰቦች ኑሮ ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠሩን በመገልፅ አልሚ ምግብን ለማግኘት አስቸጋሪ ወይም ውድ እየሆነ መጥቷል ይላል ድርጅቱ ፡፡
የበጎ አድራጎት ድርጅቱ በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ በሚገኙ የህክምና ተቋማት ውስጥ በምግብ እጥረት የሚሰቃዩ ህፃናት ቁጥራቸው እየጨመረ መሆኑንም ገልጿል ፡፡
ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊትም ከሰሃራ በታች በሚገኙ ሀገራት በጎርፍ ፣ በመፈናቀል እና በአንበጣ መንጋ ምክንያት የምግብ ዋስትና ችግር ማጋጠሙ የሚታወቅ ነው ፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ