አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአለማችን ውዱ በግ በ490 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተሸጧል።
የበጉ ሽያጭ የተካሄደው በስኮትላንድ ብሔራዊ ሽያጭ ከፍተኛ የመጫረቻ ፍልሚያ የነበረበት ነው ተብሏል።
ጨረታው የመክፈቻ 9 ሺህ ዶላር የነበረ ሲሆን፥ በፍጥነት የገንዘቡ መጠን ወደ 490 ሺህ ዶላር ከፍ ብሏል ነው የተባለው፡፡
በስኮትላንድ በዚህ ወጋ የተሸጠው ይህ በግ ቴክሰል በመባል የሚታወቀው የበጎች ዝርያ ሲሆን፥ አሁን በይፋ በዓለም ላይ በጣም ውዱ በግ መሆን ችሏል።
ዳይመንድ ተብሎ የሚጠራው ይህን በግ የገዙትም አንድ ላይ ለማራባት በወሰኑ ሶስት አርሶ አደሮች በሽርክና ነው ተብሏል።
የቴክስል የሚባሉት በጎች የሚመጡት ከሆላንድ በስተሰሜን ምዕራብ ከሚገኙት ደሴቶች አንዷ በሆነችው እና አሁን የእንግሊዝን የበግ ኢንዱስትሪ በበላይነት ከሚቆጣጠራት የቴክስል ደሴት ነው።
ከዚህ በፊት በ2009 የዚህ ዝርያ በግ በ231 ሸህ የአሜሪካ ዶላር ነበር የተሸጠው።
ምንጭ፦ howafrica.com