የሀገር ውስጥ ዜና

የብልፅግና ፓርቲ የአማራ፣ የደቡብ፣ ሶማሌና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የአመራር ስልጠና እየተካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

August 31, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብልፅግና ፓርቲ የአማራ፣ ሶማሌ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የአመራር ስልጠና እየተካሄደ ይገኛል።

የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በባህርዳር የመጀመሪያውን ዙር የአመራር ስልጠና በዛሬው እለት የጀመረ ሲሆን፥ የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ደግሞ በጅግጅጋ ከትናትናው ዕለት ጀምሮ በማካሄድ ላይ ይገኛል።