Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ51 ሺህ በለጠ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 24 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 21 ሺህ 499 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 1 ሺህ 468 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ ።

ሚኒስቴሩ በዕለታዊ መግለጫው በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 51 ሺህ 122 ደርሷል።

በሌላ በኩል 266 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 18 ሺህ 382 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በ24 ሰዓታት ውስጥም የ23 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ያንንም ተከትሎ በሀገሪቱ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 793 ደርሷል።

እንደ ሚኒስቴሩ መግለጫ በአሁኑ ወቅት 344 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት በፅኑ ታመዋል።

Exit mobile version